ኮሚቴዎች

የተሻሻለው የ ANC 4B የአሰራር ደንቦችጃንዋሪ 27 ቀን 2020 እንደተሻሻለው ኮሚሽኑ፣ ከኮሚሽኑ ጋር ተዛማጅነት ያለውን አንድ ጉዳይ ወይም ጉዳዮች ለማየት ያግዘው ዘንድ ኮሚቴዎች እንዲያቋቁም ይፈቅድለታል፡፡ ። ይመልከቱ የአሰራር ደንቦች § V(ሀ) (““እንዲህ ያለው ኮሚቴ ለሕዝብ ተሳትፎ ተጨማሪ ብቃት እንዲሁም ተጨማሪ ዕድል ሊሰጥ ይችላል፡፡”) ። እነዚህ የአሰራር ደንቦች ኮሚሽኑ በመደበኛ ሕዝባዊ ስብሰባ በአብላጫ ድምጽ በሚወሰን ውሳኔ የማንኛውንም ኮሚቴው ተግባራት እና ኃላፊነቶች እንዲሁም የአባላቱን ስብጥር እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ያስቀምጣሉ ።

በእነዚህ ደንቦች መሠረት ኮሚሽኑ የሚከተሉትን ኮሚቴዎች አቋቁሟል:-

  • የማህበረሰብ ደህንነት እና ድጋፍ ኮሚቴ –የተቋቋመው በየካቲት 26, 2024 ውሳኔ . እስከ ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን በ ኮሚሽነር ቲፋኒ ኒኮል ጆንሰን (4B06 ) ● ይመራል ። የኮሚው ሥራ ከዚህ ሚከተሉትን ያካተተ ነው፡- (1) ለማኅበረሰቡ የደህንነት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ስትራቴጂያዊ ምክረ ሃሳቦች ማቅረብ እና ከኮሚሽኑ ቁልፍ እሴቶች ጋር የሚጣጣሙትን መደገፍ፤ (2) በፖሊስ አገልግሎት እና በፖሊስ ሪፎርም ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማበረታታት፣ ነገር ግን ተለምዷዊ የሆኑ የፖሊስ አሰራር ዘዴዎች ላይ ምክንያዊ አማራጮችን መደገፍ፤ በዚህም ስር የልዩ ልዩ የደህንነት አማራጮችን፣ ፕሮግራሞን እና ምዝገባዎችን ማጠናከር ይካተታሉ፤ (3) በማኅበረሰብ ደህንነት እና ድጋፍ ሕግ እና ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ውጤት ባላቸው የሕግ እና የፖሊሲ ጉዳዮችን መከታተል፣ መተንተን እንዲሁም ግብረ መልስ መስጠት፤ (4) ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት እና በመደገፍ ማኅበረሰቡን በማኅበረሰብ ደህንነት እና የድጋፍ ጉዳዮች ላይ ማሳተፍ፤ (5) ከልዩ ልዩ ቡድኖች፣ ኤጀንሲዎች እና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት በመመስረት በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የተሻለ ማህበረሰባዊ ድህንነት እና ድጋፍ እንዲኖር ማድረግ፡፡

And acting under those Rules, the Commission established the following Committees no longer in operation:

  • የቤቶች ፍትህ ኮሚቴበውሳኔ 4B-20-0205 በበፌብርዋሪ 24 ቀን 2020 ተቋቋመ ። እስከ ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን በኮሚሽነር ኤሪን ፓልመር (4B02) ይመራል ። የኮሚተው ሥራ ከዚህ የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡- (1) የቁጠበ ቤቶችን አካትቶ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ይህንን ከሁሉ በተሻለ ከማሳካት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመወሰን በኮሚሽኑ ወሰኖች ከባቢ የቀረቡትን ልማት ሥራዎች መፈተሽ (2) በተመጣጣኝ ዋጋ የቤቶች አቅርቦት ቤት አልባዎች ላይ ውጤት ያላቸውን ረቂቅ ሕጎች እና ፖሊሲዎች መተንተን እና ግብረ መልስ መስጠት እና የዚህም ግብ የቁጠባ ቤቶችን መጨመር እና ማስፋፋት እንዲሆን ማድረግ፤ (3) በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶችን ስለማቅረብ እና ቤት አልባዎችን በተመለከተ በልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ ትምህርታዊ ዝግጀትቶች ማካሄድ እና መደገፍ

  • ራዕይዜሮኮሚቴበኦክቶበር 26 ቀን 2020 በውሳኔ 4B-20-1006 የተቋቋመ ። እስከ ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን በኮሚሽነር ኢቫን ያትስ (4B04) እና በኮሚሽነር አሊሰን ብሩክስ (4B08) በጋራ ይመራል ። የኮሚቴው ሥራ ከዚህ የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡- (1) በኮሚሽኑ አካባቢ በቪዥን ዜሮ ግቦች መሠረት የማኅበረሰቡን ደህንነት ለመጨመር የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ከግምት ማስገባት እና ምክረ ሃሳብ ማቅረብ፤ (2) እግባብነት ያላቸውን የቀረቡ ዕቅዶች እና ፕሮጀክቶች እንዲሁም ከእነዚህ ግቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ በማኅበረሰቡ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ ያላቸውን የሕግ እና የኤጀንሲ ውሳኔዎች መተንተን እና ግብረ መልስ መስጠት፤ (3) የቪዥን ዚሮ ግቦችን ለማሳካት ኮሚሽኑ በሚያደርገው ጥረት ላይ ከተጋላጭ የመንገድ ተጠቃሚዎች ወካይ የአካባቢ ቡድኖች ጋር በጋራ መሥራት ።

  • የወጣቶች አማካሪ ኮሚቴውሳኔ 4B-23-0903 ሴፕቴምበር 26 ቀን 2023 ተቋቋመ ። እስከ ሰባት የወጣት አባላትን (ዕድሜያቸው 12-18) ያቀፈ ሲሆን በኮሚሽነር አሊሰን ብሩክስ (4B08) እና በኮሚሽነር ኤሪን ፓልመር (4B02) በጋራ ይመራል ። የኮሚቴው ሥራ ከዚህ የሚከተሉትን ያካተተ ነው፡- (1) በኮሚሽኑ ወሰን ውስጥ ለሚገኙ ወይም በኮሚቴው ወሰን ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ ወጣቶች በዲሲ ውስጥ ስለ ቁልፍ አካላት እና ስለ ፖሊሲ አወጣጥ ሂደቶች ስለ ኮሚሽኑ ስለራሱ ታሪክ፣ ተልዕኮ እና ሥራ ትምህርት መስጠት፤ (2) በዲስትሪክቱ ውስጥ በወጣቶች እና ቤተሰቦች ላይ ተጽዕኖ ስላላቸው ረቂቅ ሕጎች እና ፖሊሲዎች ግብረ መልስ መፈለግ እንዲሁም የወጣቶች ድምጽ እንዲሰማ መንግሥት ወደ ተግባር ሊገባ የሚችልባቸውን ሃሳቦች ማጎልበት፤ እንዲሁም፤ (3) በኮሚሽኑ ሥራዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን ማሳተፍ፤ በእነርሱም ስር ስብሰባዎች፣ የሕዝብ አገልግሎቶት እና ሌሎች የወጣቶች ተሳትፎ ዕድሎች ይካተታሉ፡፡