አማካሪ የአካባቢ ኮሚሽን፣ ወይም ANC ከፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ አካባቢያዊ አካል ሲሆን፣ አባላቱም ከአካባቢው የተመረጡ አማካሪ የአካባቢ ኮሚሽነሮች ተብለው ይጠራሉ፡፡ የ ANC አባላት በአካባቢው እና በዲስትሪክቱ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ጉዳዮች ውይይት በማድረግ መፍትሔ ይሰጣሉ ፡፡ እነርሱም የዲስትሪክቱ ሆም ሩል ቻርተር ልዩ ገጽታ ናቸው፡፡
ያለ ደመወዝ ለሁለት ዓመት የሚያገለግሉት እነዚህ ኮሚሽነሮች በኖቬምበር ወር በዲሲ ምርጫ ውስጥ ይመረጣሉ ። ANC የተመሠረቱት መንግስት ለሕዝቡ እንዲቀርብና ሕዝቡም ወደ መንግስት እንዲቀርብ ነው ።
ANC 4B ከጆርጂያ ጎዳና ወደ ምዕራብ፣ ከኢስተርን ጎዳና ወደ ምሥራቅ፣ እንዲሁም ከሞዙሪ ጎዳና ወደ ሪግስ መንገድ፣ ሳውዝ ዳኮታ ጎዳና እና ወደ ኬኔዲ መንገድ ወደ ደቡብ ይሄዳል፡፡ በየትኛው ANC ውስጥ እንደሚኖሩእርግጠኛካልሆኑእዚህይመልከቱ ።

አውቶማቲክ ወቅታዊ የኮሚሽን መረጃዎች
እርስዎ የኮሚሽኑን እንቅስቃሴዎች በየወቅቴ ለመከታተል እንዲችሉ ANC 4B በአውቶማቲክ ዘዴ ወቅታዊ የተደፈጉ መረጃ መስጫዎችን ይይዛል፡፡
- መጪ የኮሚሽኑ ስብሰባዎች iCal ፊድ
- የመጪው የኮሚሽኑ ስብሰባዎች የጉግል የቀን መቁጠሪያ ፊድ
- የተለጠፉ አጀንዳዎች RSS ፊድ
- የተለጠፉ ቃለ ጉባዔዎች RSS ፊድ
- የተለጠፉ የፋይናንስ ሪፖርቶች RSS ፊድ
- የአጀንዳዎች ፣ ጉባዔዎች እና የፋይናንስ ሪፖርቶች RSS ፊድ
ከዚህ በታች ኢሜልዎን በማስገባት የመጪውን የኮሚሽኑ አጀንዳዎች የኢሜል ማስታወቂያ ለማግኘት መመዝገብ ይችላሉ-
ANC ስብሰባ ተደራሽነት
ANC 4B ሁሉም ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ሁሉን አቀፍ እና ተደራሽ ስብሰባዎችን ለማሰናዳት ይጥራል ። ኮሚሽኑ ዙምን ለቨርቹዋል ስብሰባዎች ይጠቀማል፤ በዚህም ሥር አውቶሜት የተደረጉ ጽሑፎች (ካፕሽኖች) የተካተቱ ሲሆኑ፣ ተሳታፊዎች በቪድዮ ወይም በድምጽ ለመናገር እንዲችሉ እጅ የማውጣት ዘዴን በመጠቀም ጥያቄ መጠየቅ እና መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንደ ቋንቋ ትርጓሜ ያሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወይም ተደራሽነትን በተመለከተ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እባክዎን ለኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና ጸሐፊ ኢሜይል ይላኩ። የሚቻልዎ ከሆነ ሁሉንም ጥያቄዎች ከ72 ሰዓታት አስቀደመው እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ ኮሚሽኑ ለስብሰባ ግልጋሎቶች የቀረቡለትን ጥያቄዎች ሁሉ ለማሟላት የኮሚሽኑ አቅም እስከሚፈቅደው ድረስ ጥረት ያደርጋል፡፡ መልዕክት ማግኘትዎን ለመተው በኢሜሉ ውስጥ ያለውን አንሰብስክራይብ ሊንክ ይጫኑ ።
