መመሪያዎች: ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች አማካሪ የአካባቢ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ቅጽ 100 መሙላት አለባቸው – ይህም ቅጽ አማካሪ የአካባቢ ኮሚሽን የገንዘብ ድጎማ ማመልከቻ ነው፤ ይህም ማመልከቻ ለ ANC 4B መቅረብ አለበት (የሚቀርበውም በኮሚሽኑ ሰብሳቢ እና ገንዘብ ያዥ አማካኝነት ነው) እናበተጨማሪምለአማካሪየአካባቢኮሚሽን በ OANCS@dc.gov ማቅረብ አለባቸው ።
*አመልካቾች ማመልከቻቸውን ከማስገባትዎ በፊት የማመልከቻ መመሪያዎችን እና የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ ከአንድ የተወሰነ ANC 4B ኮሚሽነርወይምኮሚሽነሮችጋርእንዲነጋገሩይበረታታሉ ።*
የማመልከቻ እና ፈቃድ መስጫ የጊዜ ሰሌዳ፡- አመልካቾች በአንድ ዓመት ውስጥ ለገንዘብ ድጎማ ብቁ ለመሆን ከሴፕቴምበር 30 በፎት ማመልከቻቸውን ለ ANC 4B ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኮሚሽነሮች ብቁ አመልካቾች በኮሚሽኑ የየኦክቶበር ስብሰባ ላይ እንዲያቀርቡ እና በዚያ ስብሰባ ላይ ካቀረቡ በኋላ የገንዘብ ድጎማውን ስለመስጠት ድምጽ ሊሰጡበት ይችላሉ፡፡
ኮሚሽኑ ጥብቅ የጊዜ ሰሌዳ ያላቸው፣ በዚህ የጊዜ ሰሌዳ ጋር የማይጣጣሙ የገንዘብ ድጎማ ጥያቄዎችን እንደነገሩ ሁኔታ ይመለከታል፡፡ እንዲህ ባለው ማመልከቻው ላይ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የኮሚሽኑ ነው፡፡
የገንዘብ ድጎማ የገንዘብ መጠኖች፡- ANC 4B በሴምፕቴምበር ወር የራሱን በጀት እና ጊዜያዊ የገንዘብ ደጎማ መጠኖችን ይወስናል፡፡ አመልካቾች የገንዘብ ድጎማ የገንዘብ መጠኖች ላይ ለመወያየት ከማመልከታቸው በፊት ከሚመለከተው ANC 4B ኮሚሽነር ወይም ኮሚሽነሮች ጋር እንዲነጋገሩ ይበረታታሉ ።
የኮሚሽን ግኝት ግቦች: ANC 4B በዲሲ ኮድ § 1-309.13 (ሜ)ውስጥ በተካተቱት ህጋዊ መስፈርቶች መሠረት የእርዳታ ማመልከቻዎችን ይገመግማል ፣ አመልካቹ ድርጅት በተፈጥሮው የህዝብ መሆኑን እና ድጎማ የተጠየቀበት ፕሮጀክት በANC 4B የጂኦግራፊያዊ ወሰን ውስጥ የሚኖሩ ወይም የሚሰሩ ግለሰቦችን የሚጠየቅም ስለመሆኑ ይገመግማል።
የድጎማ ተቀባይነት መስፈርቶች፡- የድጎማ ተቀባዮች የድጎማ ገንዘብ የቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በስልሳ (60) ቀናት ጊዜ ውስጥ እና ድጎማውም ጥቅም ላይ እስካልዋለ ድረስ በየዘጠና (90) ቀናቱ የድጎማ ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሪፖርቱም ለ ANC 4B (በኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና በገንዘብ ያዥ አማካኝነት) እንዲሁም OANCS@ dc.gov ለአማካሪ የአካባቢ ኮሚሽኖች በመላክ አለበት፡፡
የድጎማው ሪፖርት የድጎማው ገንዘብ በምን መልኩ ጠቅም ላይ እንደዋለ እንዲሁም ስለፕሮጀክቱ ውጤት የሚገልጽ ሊሆን ይገባል፤ በዚህም ስር ፕሮጀክቱ በምን ያህል መጠን የተቀመጡትን ገቦች እንዳሟላ፣ በፕሮጀክቱ ወቅት ያጋጠሙ ማናቸውም እንቅፋቶች ካሉ እንዲሁም ስለ ፕሮጀክቱ የረጅም ጊዜ ውጤት ማካተት አለበት፡፡
*Grant recipients are strongly encouraged to communicate with a specific ANC 4B Commissioner or Commissioners regarding their grant report prior to submitting their report.*
የድጎማ ሪፖርት አለማቅረብ አመልካቹ ወደፊት ተጨማሪ አማካሪ የአካባቢ ኮሚሽን ድጎማዎች ለማግኘት ያለውን ዕድል ይጎዳል፡፡
ቀደም ሲል የተፈቀዱ ድጎማዎች
- Resolution 4B-24-1001: Grant Award for Takoma Elementary School Parent Teacher Organization (Oct. 28, 2024) (awarding $3,000 to support community-facing and community-serving school festival that is outside on school grounds and open and advertised to the ANC 4B community);
- Resolution 4B-24-1002: Grant Award for Calvin Coolidge Alumni Association Inc. (Oct. 28, 2024) (awarding $4,000 to support a community-facing and community-serving Health 4 All Community Health Fair with a variety of age appropriate activities for community members, including fitness demonstrations, nutrition and cooking demonstrations, and health screenings);
- Resolution 4B-24-1003: Grant Award for Ward 4 Mutual Aid (Oct. 28, 2024) (awarding $6,000 for purchase and distribution of diapers, wipes, and hygiene items, as well as winter clothing to the local community);
- ውሳኔ 4B-23-1001:- ለታኮማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የወላጅ መምህራን ድርጅት የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 23, 2023) ((በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመካሄዱ እና ለ ANC 4B ማኅበረብ ክፍት ለሆኑ ለተዋወቁ ፌስቲቫሎች ድጋፍ ለማድረግ የተሰጠ $4,000)፤
- ውሳኔ 4B-23-1002:- የኢዳ ቢ. ዌልስ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ-መምህር ድርጅት የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 23 ቀን 2023) (የኢዳ ቢ. ዌልስ ተማሪዎችን ማኅበረሰብ ተኮር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ማብቂያ ፕሮጀክቶች የ$3,090 ድጎማ)፤
- ውሳኔ 4B-23-1005:- የደቡብ ማኖር የአካባቢ ማኅበር የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 23 ቀን 2023) (ለማኅበረሰቡ ስለሚሲዮን ሥራ ግንዛቤ ለመስጠት እና ለዚህ ለማኅበረሰቡ ግልጋሎት የሚሰጥ ማኀበር የድረገጽ ማሰሪያ እና ማቆያ የ$3,000 የድጎማ ገንዘብ)፤
- ውሳኔ 4B-22-1001፣ ለዋይተር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ መምህር ድርጅት የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 24 ቀን 2022) (ለSTEMscopes መገልገያዎች) (ከአንደኛ ደረጃ እስከ 5ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ከመገልገያዎች ጋር አጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርት) የ$3,000 የድጎማ ገንዘብ)
- ውሳኔ 4B-22-1002፣ ለታኮማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጆች መምህራን ድርጅት የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 24 ቀን 2022) (ማኅበረሰብን ለመገንባት ድርጅቱ በእያንዳንዱ ዓመት ለሚያወጣው ሁለት ፌስቲቫሎች ለማዘጋጀት የ$3,000 ድጎማ)፤
- ውሳኔ 4B-22-1004፣ ለላሞንድ-ሪግስ የዜጎች ማኀበር የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 24 ቀን 2022) (የማኅበሩን የኮሙኒኬሽን ሲስተም ለማሻሻል፣ ማለትም ለድረ ገጹን፣ ለዳታቤዝ ሥርዓት፣ ለኢሜል ቻናል እና ለማኅበረሰብ የግንኙነት ተነሳሽነቶችን እና ለሎችም የ$3,000 የገንዘብ ድጎማ)፤
- ውሳኔ 4B-22-1005፣ ለደቡብ ማኖር አካባቢ ማኅበር የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 24 ቀን 2022) (በእስር ላይ ላሉ ወጣቶች ለመጽሐፍት፣ ለመደበኛ የማኅበረሰብ የጽዳት ሥራዎች አስፈላጊ አቅርቦቶች፣ በቅርቡ በኖርዝ ካፒቶል መንገድ እና በኒው ሐምፕሻየር ጎዳና ለወደሙት “የደቡብ ማኖር አካባቢ” ማስታወቂያዎች ጽዳት የ$3,000 ድጎማ)፤
- ውሳኔ 4B-21-1005፣ ለኤመሪ ሃይትስ ማኅበረሰብ ማዕከል የተሰጠ ድጎማ (ኦክቶበር 25 ቀን 2021) (ለኤመሪ ሃይትስ ማኅበረሰብ ቀን ማክበሪያ እንዲሆን ለኤመሪ ሃይትስ ማኅበረሰብ ማዕከል የ$2,000 ድጎማ) ።
